loading
የፕሮፌሰር ምትኩ በላቸዉ ስንብት በወንጪ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 የፕሮፌሰር ምትኩ በላቸዉ የስንብት ፕሮግራም በወንጪ ተካሄደ፡፡በወንጪ ኃይቅ አካባቢ የሚኖሩ የማሃበረስብ አባላት በፕሮፌሰር ምትኩ በላቸዉ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸዉን ሀዘን በባህላዊ ለቅሶ ስነስርአት ገልጸዋል፡፡ የባህላዊ ስንብት ስነ ስርዓቱ የተከናወዉ በወንጪ ኃይቅ ዳር በተመሰረተና እሳቸዉ የመጽሐፍት ቤት ባስገነቡበት ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ነዉ፡፡

በዕለት ከተከናወኑት ባህላዊ የሀዘን መግለጫ ስነስርዐቶች ዉስጥ ነዉ፡፡በዕለቱ ከተከናወኑት ባህላዊ የሀዘን መግለጫ ስነስርዓቶች ዉስጥ አፈንና ፎኮርቻ ይገኙበታል፡፡ በአካባቢዉ ባህል እንዲህ አይንት ስነስርአት የሚከናወኑት ትልቅ ጀብዱ ለፈጸሙ ጀግኖች በሀገር አስተዳደር ተመርጠዉ ያገለገሉ፤ህዝብን በማስታረቅና በተለያ ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች ላይ በንቃት ለተሳተፉ ሰዎች ብቻ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በስነስርዓቱ የሀገር ሽማግሌዎች የሃያማኖት አባቶች ቤተዘመዶች መምህራንና ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ በስነስርአቱ ወቀት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ፕሮፌሰር ምትኩ በህይወት በነበሩበት ወቅት ያደረጉላቸዉን ድጋፍ በመዘርዝር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *