loading
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለፀ:: ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ2013 በጀት ዓመት ለማከናወን ባቀዳቸው ተግባራትና በአስር አመት መሪ እቅዱ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። በመድረኩም የህግ አወጣጥና አተገባበር፣ የሰብአዊ መብትና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል። በጠቅላይ አቃቤ ህግ የህግ ጉዳይ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ አሰግድ አያሌው እንዳሉት በ10 አመቱ መሪ እቅድ ውስጥ በአምስት አመት ውስጥ አዲስ ህግ የሚወጣላቸውና የሚሻሻሉ ህጎች ጥናት
ይደረጋል።

በመሪ እቅዱ አዳዲስ ህጎችን ማውጣት፣ የሰዎችን መብት ማስከበርና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን መግታት ትኩረት ይደረግባቸዋል። ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና በወንጀል ላይ የሚሳተፉ አካላትን ወደ ህግ ለማቅረብም የተጠናከረ ስራ ይከናወናል ተብሏል። ለዚህም ስኬት የባለድርሻ አካላት ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በትብብር እንዲሰሩ ሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *