የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድሮን በመጠቀም የጤና አገልግሎቶችን በፍጥነት ለማቅረብ እየመከርኩ ነዉ አለ፡፡
የድሮን ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ የጤናሴክተር በ2011ዓ.ም ሙከራ ተደርጎ ስራ ላይ ይውላልም ተብሏል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በፌስቡክ ገጻቸዉ እንዳስታወቁት
የድሮን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መሰረታዊ የሆኑ መድሃኒቶች፣ የክትባት መድሃኒት፣ ደምና ሌሎች የህክምና መገልገያዎች ለማጓጓዝ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡
ይህ በማንኛውም የአየር ፀባይ ሊሰራ የሚችል የድሮን ቴክኖሎጂ እስከ 5ኪ.ግ ክብደት ያለውን ቁስ መሸከም የሚችል ነዉ ተብሏል፡፡
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየጊዜው እየተፈጠሩ ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት ለመጠቀም የሚያስችል የመሰረተ ልማትና የፖሊሲ ማዕቀፎችን በመዘርጋት የህብረተሰቡን ህይወት ለመቀየር ሁሌም ጥረት ያደርጋል ብለዋል ዶክተር አሚር ፡፡