loading
የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፒ ኮንቴ ኢትዮጵያን በዚህ ሳምንት ይጎበኛሉ

አርትስ28/01/2011
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፒ ኮንቴ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ሁለቱ መሪዎች በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ታውቋል::

ይህም ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በቀጣይ የዲፕሎማሲ ግኑኝነታቸውን ከአውሮፓ አገሮች ጋር ለማጠናከር ማቀዳቸውን ተከትሎ የሚከናወን ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል አቶ ፍፁም አረጋ::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *