የግድቡ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያን ወደ ከፍተኛ እድገት የሚያመጣ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ::
አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012የግድቡ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያን ወደ ከፍተኛ እድገት የሚያመጣ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ::የህዳሴው ግድቡ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያን ወደ ከፍተኛ የስልጣኔና ምጣኔ ሀብታዊ እድገት የሚያመጣ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ።ምሁራኑ ለኢዜአ እንዳሉት የግድቡ ቀሪ ግንባታ ተጠናቆ የተሟላ አገልገሎት እንዲጀምር እያንዳንዱ ዜጋ ተቀናጅቶና ተባብሮ መደገፍ ይጠበቅበታል።በዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮ ሳይንስ መምህር ዶክተር አሰፋ አባሁምና የመጀመሪያው ዙር የግድቡ ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ኢትዮጵያዊያንን በጨለማ የኖረበት ታሪክ እንዲያበቃ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ነው።
ግብጽና ሱዳንም ይኸንን ተገንዝበው በአረንጓዴ አሻራና በሌሎችም የግድቡ የልማት ስራዎች ላይ ቢያግዙ ጥሩ እንደነበር ያወሱት ዶክተር አሰፋ፤ አሁንም ኢትዮጵያዊያን ከመንግስት በመተባባር ከግብ ማድረስ ይጠበቅብናል ሲሉ ገልጸዋል።የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ የአድዋ ድል ታሪክ ራሱን የደገመበት መሆኑንን የተናገሩት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የውሃና የኢንቫይሮንሜንታል ምህንድስና መምህር ዶክተር ኬይረዲን ተማም ናቸው።ከውጭና ውስጥ የሚነሱ አፍራሽ ዘመቻዎችን ወደ ጎን በመተው ግድቡ የመጀመሪያው የውሃው ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ለወሬኞቹ ትክክለኛ ምላሽ የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል::