loading
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባው የገቢዎች ሚኒስቴርን እና የተጠሪ ተቋማቱን የ2014 በጀት ዓመት የ10 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አድምጧል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ባቀረቡት ሪፖርት፥ ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ 360 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ባለፉት አስር ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥም 168 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ ገቢ ታክስ የተገኘ ሲሆን፥ 113
ነጥብ 8 ቢሊዮን ብሩ ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ የተገኘ ገቢ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ በዚህም የእቅዱን 93 ነጥብ 1 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው አቶ ላቀ በሪፖርታቸው ያመላከቱት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *