loading
የዳሽን ባንክ የጤና ሚኒስቴርን አመሰገነ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2012 የዳሽን ባንክ የጤና ሚኒስቴርን አመሰገነ::ዳሽን ባንክ ኮሮናቫይረስን በመከላከል ረገድ የጤና ባለሙያዎችንና የጤና ሚኒስቴር እየከፈሉት ላሉት መስዕዋትነት ለማመስገን ለጤና ሚኒስቴር አበባ አበረከተ፡፡

ባንኩ ጳግሜ 4 የምስጋና ቀን እንደመሆኑ በዚህ ወቅት እጅግ በሚባል ሁኔታ መስዋትነት እየከፈሉ በኮቪድ 19 የተያዙ ህሙማኖችን እያከሙ ያሉ ጤና ባለሙያዎችን ለማመስገን አበባ ለጤና ሚኒስቴር እንዳበረከተ ገልጿል::

የጤና ባለሙያዎች ግንዛቤ በመስጠት ረገድና ህሙማኖችን በማከም ረገድ እየከፈሉ ያለዉ መስዋትነት የላቀ ቢሆንም ህብረተሰብ ግን እያሳየዉ ያለዉ መዘናጋት የሚያሳስብና ራሱን መልሶ መመልከት እንደሚኖርበት የሚያመላክት መሆኑን የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስከያጅ አቶ አስፋዉ አለሙ የገለፁ ሲሆን የጤና ባለሙያዎችን በሚገባ ማመስገን እንደሚገባ ነዉ የተናገሩት::

የዳሻን ባንክ ማርኬቲንግና ከስተመር ኤክስፒሪያንስ ዳሬክተር ደግሞ አበባ ተስፋን የሚያመላክት በመሆኑ የጤና ባለሙያዎቻችን አዲስ ዓመትን በተስፋ እንዲቀበሉት መልካም ምኞት መግለጫ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸዉ ዳሽን ባንክ የጤና ባለሙያዎች እየከፈሉ ያለዉን መስዕዋትነት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ጳግሜ 4 የምስጋና ቀን በሆነበት አስቦ ምስጋና በማቅረቡ የተሰማቸዉን ደስታ ገልፀዉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ዳሻን ባንክ በቀጣይ በሚሊኒየም አዳራሽ በመገኘት በኮቪድ 19 የተያዙ ህሙማኖችንና የጤና ባለሙያዎችን ለማመስገን ምሳ ግብዣ እንዳዘገጀም ገልጿል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *