loading
የዲግሪ ተመራቂው ወጣት ቅድሚያ ለሀገር ህልውና ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገባ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013 በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ትምህርት በዲግሪ የተመረቀው ወጣት ስራ ቢያገኝም ቅድሚያ ለሀገር ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገባ፡፡ ከአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ወታደራዊ ስልጠናውን የተቀላቀለው ወጣት በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ የትምህርት ዘርፍ የድግሪ ምሩቅ ሲሆን ስራ ቢያገኝም ቅድሚያ ለሀገሬ ህልውና ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገብቶ እየሰለጠነ ይገኛል፡፡

የዲግሪ ተመራቂው ነጋ ምህረት ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ተመርቆ በሙያው ስራ ያገኘ ቢሆንም ኢትዮጵያን ከአሸባሪዎች መታደግ ይቀድማል በሚል ምልምል ወታደር ሆኖ ማሰልጠኛ ገብቷል፡፡ ብመረቅም ቅድሚያ ሰላም ይቀድማል ያለው ወጣቱ ሰላም ካለ ሁሉም ነገር ይደረስበታል ቅድሚያ ለሀገር የሚለውን አስቀድሜ ከአሁን በፊትም ስማርም እያለ ህልሜ መከላከያን በመቀላቀል አገሬን ማገልገል ነበር ብሏል፡፡ ወጣቱ ይህንን አሸባሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ሁላችንም በጋራ መነሳት አለብን ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *