loading
የደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ

አርትስ 22/02/2011

ፕሬዝዳንቷ  ለደቡብ  ሱዳን ሰላም ማብሰሪያ ፕሮግራም ላይ  በመታደም በጁባ  በጆን ጋራንግ  አደባባይ ባደረጉት ንግግር ተፈራራሚ ወገኖችንና  የደቡብ ሱዳን ህዝብን እንኳን ደስ አላችሁ  ካሉ በኋላ፤ የሽግግር ተቋም ኮሚቴ ቶሎ በማቋቋም ከቅድመ ሽግግር ሰራዎች ቶሎ ወደ ሽግግር መንግሰቱ  መቋቋም መገባት አለበት ብለዋል፡፡

ባለፈዉ አመት መስከረም ወር በአዲስ አበባ  በኢጋድ አደራዳሪነት በፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና በዶክተር ሪክ ማቻር  መካል የተደረሰዉን የሽግግር መንግስት ማቋቋም የሰላም ስምምነትከተፈረመ በኋላ በደቡብ ሱዳን ግጭት እየቀነሰ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *