loading
የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይከናወናሉ፡፡

ምሽት 4፡00 ላይ በተመሳሳይ ሰዓት በሚጀመሩት የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያዎች እንግሊዝ እና ጀርመን ምድር ላይ ይከናወናሉ፡፡

አርሰናል በኤመሬትስ ስታዲየም የስፔኑን ቫሌንሲያ የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡ የቀድሞ ክለባቸውን የሚገጥሙት ስፔናዊው አሰልጣኝ ኡናይ ኢመሪ ከመድፈኞቹ ጋር አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ቡድናቸውን እያዘጋጁ ሲሆን በጉዳት ምክንያት ከውድድር ዓመቱ ውጭ የሆኑትን የአሮን ራምሴ እና ዴኒስ ሱዋሬዝን ግልጋሎት በምሽቱ አያገኙም፡፡

ሜሱት ኦዚል ደግሞ የቡድኑ ስብስብ ውስጥ መካተቱ ተነግሯል፡፡

ቼልሲ ደግሞ ወደ ጀርመን አምርቶ አይንትክራፍት ፍራንክፈርትን ኮሜርዝ ባንክ አሬና ላይ ይጎበኛል፡፡

በተከላካይ ዕጦት ችግር ውስጥ እንደሚገኙ እየተናገሩ የሚገኙት አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ፤ በምሽቱ የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ የአንቶኒዮ ሩዲገር እና ጋሪ ካሂል ጉዳት ላይ መሆን ተከትሎ፤ አሰልጣኙ አምበሉን ሴዛር አዝፒሊኮይታን ጨምሮ ሁለት የመሀል ተከላካይ (ዳቪድ ሊዊዝ እና አንድሪያስ ክርስቲያንሰን) ብቻ ነው አማራጭ ያላቸው ተብሏል፡፡

በተያዘው የዩሮፓ ሊግ የውድድር ዓመት ሽንፈት የማያውቃቸው ሰማያዊዎቹ፤ ስላቪያ ፕራሃን በሩብ ፍፃሜው ጥለው እዚህ ደረጃ ላይ ሲገኙ፤ ፍራንክፈርት ደግሞ በቡንደስሊጋው አራተኛ ደረጃ ላይ ተገኝቶ በዩሮፓ ሊጉ 11 ጨዋታዎች ሜዳው ላይ አልተሸነፈም፡፡

በሩብ ፍፃሜውም የፖርቱጋሉን ቤንፊካ ውጤት ቀልብሶ ይሄንን ዙር ተቀላቅሏል፡፡

በምሽቱም ይሄንን ክብራቸውን ለማስጠበቅ ይተጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *