loading
የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት የሴቶን ጥቃት ለሚዋጉት ተሰጥቷል

አርትስ 25/01/2011
ሽልማቱን በጋራ የወሰዱት ኢራቃዊቷ ናዲያ ሙራድና ኮንጓዊው ዶክተር ዴኒስ መኩዌጅ ናቸው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ሁለቱም የሽልማቱ አሸናፊዎች ለዚህ የበቁት በጦርነት ወቅት የአስገድዶ መደፈር እና ሌሎች ጥቃቶች የሚደርስባቸውን ሴቶች ለመታግ ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ነው፡፡
ናዲያ ባደረገቻቸው የቅስቀሳ ዘመቻዎች ሁሉ የአይ ኤስ አይ ኤስ ወታደሮች ያደረሱባትን ወሲባዊ ጥቃት ለአብነት በመጥቀስ ለዓመታት ስታስተምር ቆይታለች፡፡
የፅንስና ማህፀን ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ዴኒስ በበኩላቸው መደፈር የደረሰባቸውን ሴቶች በሞያቸው ከመርዳት በሻገር በተለይ የሀገራቸው መንግስት ሴቶችን ከጥቃት እንዲታደግ ፊት ለፊት ተጋፍጠውታል፡፡
ሁለቱ ግለሰቦች በጦርነት ወቅት ፆታዊ ጥቃትን እንደ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም እንዲቆም ባደረጉት ጥረት በሚል ዘርፍ ነው የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልባት አሸናፊዎች የሆኑት ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *