loading
የዓለም መሪዎች ምድራችንን በጋራ ለመጠበቅ ተስማሙ

የዓለም መሪዎች ምድራችንን በጋራ ለመጠበቅ ተስማሙ

አርትስ 07/ 04 /2011

መሪዎቹ ለሁለት ሳምንታት በጉዳዩ ዙሪያ ሲነታረኩ ሰንብተዋል፡፡ በመጨረሻ ግን የዓለም ሙቀት አደንዳይጨምር ሀላፊነትን ለመወጣት በሚያስችሉ ህጎች ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም የፓሪሱን ስምምነት ጨምሮ ያሉት ህጎች በቂ አይደሉም የሚለውን ሀሳብ የሚያራምዱ ወገኖች በርካታ ናቸው፡፡
ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ፖላንድ ባስተናገደቸው ጉባኤ ከ190 በላይ የሚሆኑ የሀገራት ተወካዮች ኮፕ 24 እየተባለ የሚጠራውን የፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ህግ ለመተግበር ተስማምተዋል፡፡
በዓለም ሙቀት መጨመር ሳቢያ በየጊዜው የሚደርሱትን የተፈጥሮ አደጋዎች ቆም ብሎ ማሰብና ዓለምን ለመታደግ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል የሚለው ሀሳብ በውይይቱ ወቅት ጎልቶ ወጥቷል፡፡
በጉባኤው የቀረበ ሪፖርት እንደሚያሳየው ዓለማችን የሙቀት መጠንን በ1.5 ዲግሪ ሴልሽየስ ለመቀነስ የሚለውን የፓሪሱን ስምምነት ለመተግበር 12 ዓመት ብቻ ነው የቀራት፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ይህ ሪፖርት ትልቅ የማንቂያ ደወል እነደሆነ ሁሉም ሊረዳ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ጉቴሬዝ ችግሩ እኛ ከምናስበው በላይ በመፍጠን ላይ መሆኑን ልብ ካላልን ዓለማችን የማትወጣው ችግር ውስጥ እንደምትወድቅ አትጠራጠሩ የሚል ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዋና ፀሀፊው ስምምነቱን አልፈልግም ያለችውን አሜሪካን ለመንካት በሚመስል አነጋገር ይህን ስምምነት አለማክበር በሞራል ዝቅ ማለት እና እራስን እንደማጥፋት ይቆጠራል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *