loading
የዐረብ ሊግ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ለመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄ አቀረበ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2013  የዐረብ ሊግ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ለመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄ አቀረበ፡፡በጋዛ የተቀሰቀሰው ግጭት እንዲቆም እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ድርድሩ ሂደት ዳግም እንዲጀመር ነው ሊጉ ጥሪ ያቀረበው፡፡

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በፈረንጆቹ ግንቦት 20 በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ዙሪያ ለመምከር ቀጠሮ መያዙን በድርጅቱ የአረብ ሊግ ተወካይ መጅድ አብደልፈታህ ተናግረዋል፡፡

ተወካዩ አህራም ዊክሊ ለተባለው ሳምንታዊ ጋዜጣ እንደተናገሩት የአረብ ሊግ በጋዛ ሰርጥ በእስራኤልና በሃማስ መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማስቆም ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ተግቶ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበውን ጥያቄ ተግባራዊ ማድረግ ተስኖታል ምክንያቱ ደግሞ ሀሳቡ በአሜሪካ ተቀባይነት ስለሌለው ነው ሲሉም ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን ጥቃት አሜሪካ ራስን መከላከል ነው በማለት ያሳየቸው ድጋፍ ትልቅ ስህተት መሆኑንም የአረብ ሊግ አሳስቧል፡፡
በጋዛ የቀሰቀሰው ግጭት እያስከተለ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ዓለም ዳር ቆሞ መመልከት ሳይሆን ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረግ እንዳለበትም ከአረብ ሊግ በኩል ጥሪ ቀርቧል፡፡
ለዚህ ደግሞ በቀጠናው ያሉት ተዋናዮች ቀጥተኛ ውይይት በማድረግ ፖለቲካዊ መፍትሄ ማምጣት እንዲችሉ የሁሉንም እገዛ ይፈልጋል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *