የወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢጋድ የሚኒስትሮች ካውንሰል ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ጅቡቲ ተጓዙ
የወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢጋድ የሚኒስትሮች ካውንሰል ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ጅቡቲ ተጓዙ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በ46ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ጅቡቲ ተጉዘዋል።
ስብሳባው የካቲት 20 እና 21 ቀን 2011 ዓ.ም የአባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተገኙበት በጅቡቲ የሚካሄድ ሲሆን የኢጋድ አሰራርን ለማዘመን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ድርጅት ጀቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ዩጋንዳን በአባልነት ያቀፈ ደርጅት ነው ።
የአሁኑ የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የሚመራ እንደሆነ ተገልፃôል።