loading
የኮተቤ ሜትሮፖሊቲያን ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች የመማር አቅም ለሌላቸው 100 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን እና አልባሳትን ሰጡ

አርትስ 04/01/2011

የኮተቤ ሜትሮፖሊቲያን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሀነ መስቀል ጠና የመማር አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለተማሪዎቹ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ማህበረሰባዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የተደረገ ድጋፍ ነው ብለዋል፡፡

መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም የተጀመረውን የበጎ ፍቃድ ተግባር ወደ ፊት በማስቀጠል እና በከተማዋ የተጀመረውን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ በጥናት እና ምርምር ስራዎች በማስደገፍ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *