loading
የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀመሮ በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ትምህርት ወይም ሰልፍ ለርኒግ መጨመሩን የደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ28፣ 2012  የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀመሮ በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ትምህርት ወይም ሰልፍ ለርኒግ መጨመሩን የደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፁ::ሰልፍ ለርኒግ ወይም እራስን በራስ የማሰተማር ስራ የኮቪድ 19 በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀምሮ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች መታየቱን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡ዓለማት እራስን በራስ ከማስተማር ጋር ተያይዞ ረዥም ርቀት መጓዛቸውን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ እንደ እትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት ግን እምብዛም አለመሆኑን ነው የገለፁት፡፡

ነገር ግን ይላሉ ሃለፊው፤ በሀገራችን ከቮድ 19 ከተከሰተ ግዜ ጀምሮ ዩንቨርስቲዎች ባላቸው አቅም ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ነው የደብረታቦር ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው የገለፁት፡፡እራስን በራስ በማስተማር ቴክኖሎጂ በደብረ ተቦር የሚገኙ የኮምፒውተር ሳይንስ መምህራን ከራሳቸው አልፈው ለሁለተኛ ደረጃና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና እረሳቸውን የሚያዘጋጁበት ቴክኖሎጂ መፍጠራቸውን ነው ያነሱት፡

በመምህራኖቹ የተፈጠረው አዲስ ቴክኖሎጂ ከዚህ ቀደም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተፈተኑበት የትምህርት አይነቶችን የያዘ እና በቀላሉ በእጅ ስልክ አማካኝነት ማየት የሚያስችል ሲሆን ምንም አይነት የኢንተርኔት ግንኙነት የማይፈልግ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡የደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ የ2013 ዓ.ም የተሳካ የትምህርት ዘመን እንዲሆን እና ኮቪድ 19 ያስከተለውን የትምርትህር ክፍተት ለመሙላት የገፅ ለገፅ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት ማድረጋቸውንም ከሃለፊው ጋር አርትስ ቲቪ በነበረው ቆይታ ሰምቷል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *