loading
የኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ኡሁሩ ኬንያታ ሀገሪቱን በተሳሳተ መንገድ እየመሯት ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 የኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ኡሁሩ ኬንያታ ሀገሪቱን በተሳሳተ መንገድ እየመሯት ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡
ኡሁሩ የአመራር ብቃት የላቸውም ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለዚህ አንዱ ማሳያ እሳቸው ወደ ስልጣን ሲመጡ የነበረው የመንግስት የብድር መጠን ከ17 ቢሊዮን ወደ 63 ቢሊዮን ዶላር ማሻቀቡ ነው ብለዋል፡፡


የሁለቱ መሪዎች መቃቃር የተጀመረው ኡሁሩ ከቀድሞው ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ ጋር የጀመሩትን ጥምረት ተከትሎ መሆኑን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ኡሁሩ ከኦዲንጋ ጋር ሽርክ የሆኑበት ምክንያት ደግሞ ለሦስተኛ ጊዜ መወዳደር ስለማይችሉ የፕሬዚዳንቱን ቦታ በሲስተም ለኦዲንጋ በማስተላለፍ እሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ዳግም ስልጣን ላይ መቆየት ስለሚፈልጉ ነው ተብሏል፡፡


በመጭው ምርጫ ዩናይትድ ዲሞክራቲክ አሊያንስ የተባለ ፓርቲ ወክለው በእጩነት የቀረቡት ሩቶ ምርጫውን አሸንፌ በትረ ስልጣኑን ከያዝኩ ኡሁሩ ያበላሹትን አስተዳደር ለመጠገን አንድ ወር አይፈጅብኝም በማለትም ፎክረዋል፡፡ ኡሁሩ ምርጫ አሸንፈው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ የገቡትን ቃል በማጠፍ የመንግስት ተቋማትን
የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለማሳደድ ተግባር ተጠቅመውባቸዋል ሲሉም ከሰዋቸዋል፡፡

የቀድሞዎቹ ተቀናቃኞችና አሁን ላይ በጋራ ለመስራት የተስማሙት ሁለቱ ፖለቲከኞች ይህን እቅዳቸውን ለማሳካት ህገ መንግስት እስከማሻሻል እንደሚደርሱ ነው የተነገረው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *