loading
የካናዳ መንግስት ኢትዮጵያ እየተጓዘች ያለችበትን የዴሞክራሲና የልማት ለዉጥ ጉዞ እደግፋለሁ አለ፡፡

አርትስ 07/03/2011
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከካናዳ መንግስት ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር
ማሪ ክሎድ ቢቦን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነዉ የካናዳ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት ያለዉን ድጋፍ
የገለጸዉ፡፡
በውይይቱ ሚኒስትሯ የካናዳ መንግስት ኢትዮጵያ እየተጓዘች ያለችበትን የዴሞክራሲና የልማት ለዉጥ
ጉዞ እንሚደግፍ አስታውቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ የምታደርገውን የልማት ጥረቶች የካናዳ መንግስት
በመደገፉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በቅርብ ጊዜ ውስጥም የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ ብለው
እንደሚጠብቁም፥ መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *