loading
የኩፍኝ በሽታ በአፍሪካ በአስር እጥፍ ጨምሯል፡፡

የኩፍኝ በሽታ በአፍሪካ በአስር እጥፍ ጨምሯል፡፡

ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት በሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው የኩፍኝ በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በሶስት እጥፍ ጨምሯል፡፡

አሶሸትድ ፕሬስ የድርጅቱን ሪፖርት ጠቅሶ እንደዘገበው የበበሽታው ስርጭት በአፍሪካ ብቻ ተነጥሎ ሲታይ በአስር እጥፍ ነው የጨመረው፡፡

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ክርስቲያን ሊንድሜር ጄኔቫ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህ ክስተት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2006 ወዲህ የታየ ትልቅ ቁጥር ነው ብላል፡፡

በሽታው በብዛት ተሰራጭቶባቸዋል ተብለው የተመዘገቡት ሀገራት ከአፍሪካ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ እና ማዳጋስካር ከምስራቅ አውሮፓ ደግሞ ዩክሬን ናቸው፡፡

አንዲያም ሆኖ ማዳጋስካር በቅርብ ወራት ባደረገቸው ብሄራዊ የክትባት ዘመቻ የታማሚዎችን ቁጥር መቀነስ ችላለች ነው የተባለው፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *