የእስራኤል ሴቶች ዝምታው ይሰበር እያሉ ነው
የእስራኤል ሴቶች ዝምታው ይሰበር እያሉ ነው
አርትስ 27/03/2011
ቴል አቪቭ ውስጥ የሚገኘው የራቢን አደባባይ የቤት ውስጥ ጥቃትን በሚቃወሙና በቁጣ በተሞሉ እንስቶች ተጨናንቆ ታይቷል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በዚህ ዓመት ብቻ በእስራኤል 24 ሴቶች በትዳር አጋሮቻቸው፣ በዘመዶቻቸው አልያም በቅርብ ጓደኞቻቸው በደረሰባቸው ጥቃት ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፡፡
እነዚህን የጥቃት ሰለባወች ለማሰብና ድርጊቱ እንዲቆም ለመቃወም የወጡ 30 ሺህ ሴቶች የ24 ደቂቃ የህሊና ፀሎት አድርሰዋል፡፡
ሰልፈኞች ጎዳና በወጡበት ወቅት መንገዶች ተዘጋገትው ነበር፤ ቀያይ ባሉኖችን ከፍ አድገው እያሳዩ የሴቶች ደም ተረስቶ አይቀርም የሚል መፈክርምያሰሙ ነበር፡፡
በዛሬው ዕለት ታሪክ ሰርተናል ያሉት ለተቃሞው አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች ከእንግዲህ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በዝምታ አናልፈውም ብለዋል፡፡
የተቃውሞ ሰልፉን ለማድረግ ይበልጥ የተነሳሱት ባለፈው ሳምንት ሁለት ታዳጊ ልጃገረዶች መገደላቸውን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል ሰልፈኞቹ፡፡