loading
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ቃለ መሃለ ፈፀሙ

አርትስ 15/02/2011

የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 2ኛ ልዩ ስብሰባ  የዶክተር ሙላቱን  መልቀቂያ  ተቀብሎ

በምትካቸው  አምባሳደር  ሣህለ ወርቅ ዘውዴን   ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት  ሣህለ ወርቅ ዘውዴ  ቃለ መሃለ በፈፀሙበት ወቅት የጀመርነው የለውጥ ጉዞ  በሴቶች እና በወንዶች እኩል ተጠቃሚነት  ከተመራ በእኩል የምንኖርባት ኢትዮጵያን  እውን እናደርጋለን ፤ እርስ በርስ በመፈቃቀር  እና በመከባበር  አድነታችንን በሚያጠነክሩ ጉዳች ላይ  መጠንከር ይገባናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በዳበረ በቤተ እምነታችን እና በሽምግልና  ጥበባችን ችግሮቻችንን መፍታት ይጠበቅብናል በማለት  በአፍሪካ ባልተለመደ መልኩ ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁትን የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳን ዶክተር ሙላቱን  አክብረው  ለዚህ ስልጣን  የመረጣቸውን ህዝብ አመስግነዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *