loading
የኢትዮ -ጊኒ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰበ  ተጀመረ፡፡

የኢትዮ -ጊኒ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰበ  ተጀመረ፡፡

የኢ.ፌ.ዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የጊኒ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ማማዲ ቱሬ በተገኙበት በዛሬው እለት የሁለቱ አገሮች የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ በይፋ ተጀመሯል።

የኢ.ፌ.ዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የጊኒ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ማማዲ ቱሬ የሁለቱን አገሮች የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን መመስረቻ ስምምነት ፈርመዋል።

በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተገኙበት የከፍተኛ ኤክስፐርቶች ቃለ ጉባኤ ስምምነት የተፈርሟል

ሁለቱ አገሮች በቀጣይ በጋራና በትብብር ሊሰሩ በሚገባቸው የሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማረግ በሚኒስትሮች የሚፈረሙ በርካታ ሰነዶችን ፤ በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈረሙት  የሁለትዮሽ ግንኝነት ስምምነት እና የአየር አገልገሎት ስምምነት አፈፃጸም ተገምግሟል።

በቀጣይ ሁለቱ አገሮች የትምህርት፣ ጤና፣ የፋይናንስና ማኔጅመንት፣ የግብርና፣ የባህልና ቱሪዝም መስኮች ለመተባበር የሚያስችሉ ስምምነቶች ይፈረማሉ።

ኢትዮጵያና ጊኒ ሪፐብሊክ የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን የመሰረቱት በ1950 ዓ.ም መሆኑ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *