loading
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ጉዳይ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ጉዳይ

 

በኢትዮጵያ ወንዶች ኘሪሚየር ሊግ 1ኛ ዙር 13ኛ ሳምንት ኘሮግራም ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ሳይካሄድ የቀረው የድሬዳዋ ከተማ እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ  በ1ኛ ዙር መርሃ ግብር ውስጥ መጠናቀቅ ያለበት በመሆኑ የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት እንዲካሄድ መወሰኑን የሊግ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

በተያያዘ…

በኢትዮጵያ ወንዶች ኘሪማር ሊግ 15ኛ ሳምንት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቅዳሜ የካቲት 2 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ የተገለፀው ጨዋታ፤ በተለያየ ምክንያት የውድድር ኘሮግራም ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም በመቀሌ ስታዲየም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት የሚከናወን መሆኑን የሊግ ኮሚቴ አስታውቋል ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአርትስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *