loading
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር አባላት የጠቅላይ ሚኒስትሩን የለወጥ አንድ ዓመት አደነቁ፡፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር አባላት የጠቅላይ ሚኒስትሩን የለወጥ አንድ ዓመት አደነቁ፡፡

ከተቋቋመ 7 አመት የሞላው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ከ15 ሺ እስከ 18 ሺ የሚገመቱ አባለት ያሉት ሲሆን አባላቶቹ ከቅርብ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በመደገፍ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አብረው እንደሚቆሙ ገልፀዋል፡፡

ማህበሩ በሰጠው መግለጫ የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ እድሪስ መሀመድ እንደተናገሩት በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  በአንድ ዓመት ዉስጥ ያመጡትን ለውጥ ማህበሩ ያደንቃል ፡፡

ማህበሩ በተለይም ከሀገር ውጭ  በስደት የሚኖሩ  ወደ ሀገራቸው ገብተው በሀገራቸው ጉዳይ ላይ መሳተፍ መቻለቸው  የኢትዮጵያ ዲያሰፖራ ማህበር በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚገኙ  ኢትዮጵያውያን  እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን የዲፕሎማሲ ስራዎችን እንዲሰሩ በር እንደከፈተላቻው   ሃላፊው  ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ  በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች እንዲረግቡ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ መንግስት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት የማህበሩ አባል ዶክተር ያሲን ረጁ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ከውጭ ሀገራት በርካታ ስራዎችን  የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስመጣት  ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም ስምተናል፡፡

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *