የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መጠን ባለፉት ስድስት ወራት ከሶስት እጥፍ በላይ ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መጠን ባለፉት ስድስት ወራት ከሶስት እጥፍ በላይ ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ
አርትስ 22/02/2011
የዓለም ባንክ አሁን ለኢትዮጵያ ካጸደቀው የበጀት ድጋፍ ባሻገር ከሶስት ወራት በኋላ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ለመጨመር ቃል መግባቱንም ይፋ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ትናንት በጀርመኗ ፍራንክፈርት ከተማ አሬና ስታዲየም ውስጥ ከአውሮፓ ሃገራት ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ጋር በነበራቸው ቆይታ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዳሉት የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መጠን ከነበረበት እጅግ ዝቅተኛ አሃዝ ተላቅቆ ባለፉት ስድስት ወራት የ334 በመቶ እድገት አሳይቷል።
የዓለም ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍ ለኢትዮጵያ ማጽደቁ የምንዛሪ እጥረቱን ለመቀነስ እንደሚያስችልም ነው የተናገሩት።
ባንኩ በኢትዮጵያ በኩል የቀረበለትን ተጨማሪ የድጋፍ ጥያቄ በማጤን ከሶስት ወራት በኋላ ሶስት ቢሊዮን ዶላር ለመጨመር ቃል መግባቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ውይይት ላይ ይፋ አድርገዋል።