loading
የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ከ40 ዓመታት በኋላ የሞቃድሾ በረራውን ጀመረ

የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ከ40 ዓመታት በኋላ የሞቃድሾ በረራውን ጀመረ

አርትስ 30/02/2011

የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ከ40 ዓመታት በኋላ የሞቃድሾ በረራውን በዛሬው ዕለት ጀምሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞቃድሾ በራራ መጀመሩን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየርር መንገድ ዋና ስራ አስፋፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም እንደገለጹት አየር መንገዱ ከ40 ዓመታት በኋላ የሞቃዲሾ በረራውን እንደገና መጀመር የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝግ ግንኙነት እና ንግድ ያጠናክራል ብለዋል።

በመላው ዓለም የሚገኘውን የሶማሊያ ዲያስፖራ ከሀገሪቱ በመገናኘት ሶሚሊያን እንደገና በመገንባት ሂደት ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ነው የገለጹት።

ከዚህም ሌላ ሀገሪቱ ወደ ተለያዩ የዓለም አካበቢዎች የምትልከውን የአሳ ምርት ጨምሮ ሌሎች የወጭ ምርቶችን ለመላክ የካርጎ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

ሶማሊያ የኢትዮጵያ የንግድ አጋር መሆኗን ያመለለካቱት ዋና ስራ አስፈጻሚው በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ከአራት አስርት አመታት በኋላ የአየር መንገድ አገልግሎቱ መጀመር አሁን ላይ በቀጠናው እየተፈጠረ ያለውን ሰላም እና አንድንነት የበለጠ እንደሚያጠናክረውም አስረድተዋል።

በተመሰሳሳይ መልኩ ካለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ተቋርጦ የነበረው የአየር መንገድ ግንኙነት ባሳለፍነው ነሃሴ ወር እንደገና መጀመሩንም አስታውሰዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *