loading
የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፤ በህገወጥ መልኩ ለህብረተሰቡ ሊሸጥ የነበረ የኮልጌት ምርት ይዤያለሁ አለ

አርትስ 18/04/2011

ባለስልጣኑ ተመሳስሎ የተሰራውን ኽርባል ኮልጌት በቁጥጥር ስር ያዋለው፤ ከፌዴራል ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት፣ ኢንተር ፖል እናየአዲስ አባባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ነው፡፡

ባለስልጣኑ እንዳለው ወንጀሉ የተደረሰበት አንድ የኮስሞቲክስ አምራች ድርጅት ዴንታል ፕላስ የተባለውን ህጋዊ መድኃኒት በማስመሰል 330 የፕላስቲክ ጠርሙስ ኽርባል ኮልጌት የተባለ ተመሳስሎ የተሰራ መድኃኒት በህገወጥ መልኩ በሽያጭ ሰራተኛው አማካይነት ሲያሰራጭ፤ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል ነው፡፡

መድሀኒቱ በባለስልጣኑ ያልተመዘገ እና ፍቃድም ያልተሰጠው ነዉ፡፡

ባለስልጣኑ ኽርባል ኮልጌት የተባለ ተመሳስሎ የተሰራ መድኃኒት ፣በባለስልጣኑ ያልተመዘገ እና ፍቃድም ያልተሰጠው ፣የመጠቀሚያ ጊዜያልተገለጸ ፣ምንነቱ በላብራቶሪ ጥራት ምርመራ ያልተረጋገጠ እና በህጋዊ መልኩ የተመዘገበ ምርትን አመሳስሎ እንዲሁም የተሳሳተ የስልክቁጥር ያስቀመጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም የምርቱ ምንነት ያልታወቀና ከፍተኛ የጤና ጉዳቱ ሊያስከትል ስለሚችል እንዲሁም ምርቶቹ በተለያዩ ክልሎች እና የመድኃኒትችርቻሮ ድርጅቶች የተሰራጨ በመሆኑ ህብረተሰቡ መድኃኒቱን እንዳይጠቀምና ማንኛውም ድርጅት ምርቶቹን ሲሸጥ ወይም ሲያከፋፍልቢገኝ በባለስልጣን መስሪቤቱ የነጻ የስልክ መስመር በ8482 እንድታሳውቁኝ ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *