የኢትዮጵያ የሒሳብ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ሊቋቋም ነው
የኢትዮጵያ የሒሳብ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ሊቋቋም ነው
አርትስ 28/03/2011
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የአፍሪካ የሒሳብ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በጋራ ያዘጋጁት የሴት ሒሳብ ባለሙያዎች አውደ ጥናት ‹‹ሴቶች በሂሳብ ሳይንስ ዘርፍ እንዲሰማሩ መሳብ›› በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል፡፡
አውደ ጥናቱ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ በሂሳብ የላቀ እውቀት ያላቸው ሴቶች ተሳትፈውበታል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ወ/ማርያም እንደተናገሩት አውደጥናቱ ከመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ ሴቶች በሂሳብ ትምህርት ፍላጎት እንዲኖራቸው ለማድረግ እና በአፍሪካ ሀገራት በሂሳብ ትምህርት ዘርፍ ያሉ ሴቶች ተሞክሮ እንዲለዋወጡ የሚያግዝ ነው፡፡
ጨምረውም ሴቶችን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነርሪንግ እና ሒሳብ ዘርፎች ማሳተፍ የአፍሪካንም ሆነ የአለም ችግር እንደሚፈቱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ሴት ተማሪዎችን በዘርፉ ለማሳተፍ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አንደሚጠቁመው በዘርፉ የላቀ እውቀት ያለቸውን ሴቶች በመለየት የኢትዮጲያ የሒሳብ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በቅርቡ ይቋቋማል፡፡