loading
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ጥሪ አቀረቡለት

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ወደሀገሩ እንዲመለስ መጋበዛቸውን ያስታወቁት።
በመግለጫቸውም በሪዮ ኦሎምፒክ እና በልዩ ልዩ የዓለም አትሌቲክስ መድረኮች በመሳተፍ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አስተዋጽኦ ያበረከተው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ፍላጎታቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጁት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለአትሌት ፈይሳ የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉም ገልፀዋል፡፡
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2016 በብራዚል በተካሄደው የሪዮ ኦሊምፒክ ሀገሩን ወክሎ በማራቶን ውድድር መሳተፉ ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *