የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት መስጠት መጀመሯ ይጠቅመኛል አለ
አርትስ 23/02/2011
የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለአርትስ እንደተናገሩት፤ አየር መንገዱ የአገልግሎት አድማሱን ከማስፋት ጎን ለጎን ዘመናዊ አሰራርን በማስፈን በአፍሪካ የአቪዬሽን ኢነዱስትሪ መሪነታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
አቶ ተወልደ ለአፍሪካ ሀገራት የቪዛ አገልግሎቱ መሰጠት መጀመሩ ደሞ አየር መንገዱ የበለጠ ተቀባይነቱ እንዲያድግ ያደርገዋል ይላሉ፡፡
አገልግሎቶቹን ከማዘመን ጎን ለጎን በአይነትም በመጨመር ለተጠቃሚው መደላደልን ለመፍጠር ዝግጀት ማጠናቀቁም ተናግረዋል፡፡ አገልግሎቱን ቀድመው ከጀመሩ 3 ሃገራት ጋርም በቂ የሚባል የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸዉንም ገልጸዋል፡፡
ስራ አስፈጻሚዉ አየር መንገዱ ካሁን በፊት የኦን ላይን ቪዛ አገልግሎትን ሲሰጥ የነበረው ለተወሰኑ የአፍሪካ ሃገራት ብቻ እንደ ነበር አስታውሰው፤ አሁን ግን ሀሉም የአፍሪካ አህጉር ነዋሪ በፈለገበት ጊዜ በቀላሉ አገልግሎቱን እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዉናል፡፡
ይህም አየር መንገዱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደሚጠቀምና ከሌሎች የአለም ሃገራት ጋር ያለው ትስስር እንዲጎለብት ያደርገዋል ብለዋል፡፡