loading
የኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ በይፋ ስራውን ጀመረ

አርትስ 13/02/2011

በቀን አንድ ዶላር እናዋጣ በሚል የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጥሪ ተከትሎ በውጪ ሃገራት በሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን   የተቋቋመው  የኢትዮጵያ  ዲያስፖራዎች ትረስት ፈንድ  በትላንትናው ዕለት በይፋ ስራውንጀምሯል፡፡

ትረስት ፈንዱ በርካታ ታዋቂ ሰዎችን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን  ለስራው ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ ትላንት በይፋ ገንዘብ ማሰባሰብ ጀምሯል።

የገንዘብ ድጋፉ በሀገር ቤት  ለሚኖሩ እና ለተቸገሩ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት የሚውል ሲሆን  በ www.ethiopiatrustfund.org ድጋፍ የማድረጊያ ድረ ገፁ መሆኑም ይፋ ተደርጓል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *