loading
የኢትዮጵያ ሳምንት በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 የኢትዮጵያ ሳምንት በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው። በ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት በ 3 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተዘጋጀው ፌስቲቲቫሉ ሀገሪቱ ያላትን ሀብትና የተፈጥሮ ፀጋ ለማስተዋወቅ እንዲሁም ወደ ኢንቨስትመንት አማራጭ ለመለወጥ ያለመ ነው። በፌስቲቫሉ ላይ የተለያዩ ክልሎች ልዩ መገለጫችን ያሉትን ባህላቸውን እያስተዋወቁበት ይገኛሉ።

መሰል ፌስቲቫሎች ከሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር መዘጋጀታቸው ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣትና አንድነትን ለማጠናከር ጎልህ ሚና እንዳለው አርትስ ያነጋገራቸው የተለያዮ ክልሎችን ወክለው የተገኙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል። ክልሎች ልዩ መገለጫችን ነው ያሉትን ባህላቸውን በተለያዩ ቅርፃ ቅርፆች: በተንቀሳቃሽ ምስሎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ጭፈራዎችን ዝግጅቱን ለመታደም ለመጡ ታዳሚያን እያሳዩም ይገኛሉ ። በዝግጅቱ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፌዎች ተገኝተዋል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *