loading
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በታህሳስ ወር 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ምርቶችን ማገበያየቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በታህሳስ ወር 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ምርቶችን ማገበያየቱን አስታወቀ።

የምርት ገበያ 39 ሺህ 240 ቶን ሰሊጥ፤ 27 ሺህ 773 ቶን ቡና  እና 10 ሺህ 995 ቶን  ነጭ ቦሎቄ ነው ማገበያየቱን የገለጸው፡፡

ሰሊጥ ከግብይት መጠኑ 51 በመቶ በመሸፈን የመጀመሪያው ሲሆን፥ በዋጋ ደረጃ ደግሞ ቡና 40 በመቶ በመያዝ ቀዳሚ መሆኑን ጠቅሷል።

ቡና ከባለፈው ወር ግብይት ጋር ሲነፃፀር በመጠን የ29 በመቶ በዋጋ ደግሞ የ36 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ሰሊጥ በመጠን ከባለፈው የ22 በመቶ ዕድገት ሲያሳይ በዋጋ ደግሞ 27 በመቶ ጨምሯል።

ነጭ ቦሎቄ እንዲሁም 36 በመቶ በመጠን ዕድገት ሲያሳይ በዋጋ 50 በመቶ ከባለፈው ወር ጭማሪ ማስመዝገቡን በላከው መረጃ ገልጿል ።ዘገባው የፋና ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *