የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ
የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ
ለ20 ዓመታት ከሃገር ውጭ የነበሩ የኢሳት ቴሌዥን ጋዜጠኞች በዛሬ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡
የኢሳት ጋዜጠኞቹን የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳሁን እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት አቀባበል አድገውላቸዋል።
በተጨማሪም የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎቻቸው እና ደጋፊዎቻቸውም ጭምር በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
ጋዜጠኞቹ በበኩላቸው ወደ ሃገራቸው በመግባታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው እና በሃገሪቱ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል እና የሚዲያ ሃላፊነቱን ለመወጣት ጠንክረው እንደሚሰሩ ለኢቢሲ አስታውቀዋል።