የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ 7 የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ተጠናቀቀ
አርትስ 25/01/2011
የአቋም መግለጫውን ያቀረቡት ጓድ ንጉሱ ጥላሁን ሲሆኑ የመግለጫው ነጥቦችም ፦
• በአገራችን ህዝቦች አነሳሽነት ኢትዮጵያ ወደ ለውጥ ምዕራፍ ገብታለች፡፡ እኛ የጉባኤው ተሳታፊዎች ለውጡ እንዳይቀለበስ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለብን ከመግባባት ላይ ደርሰናል፡፡
• ዲሞክራሲን በማስፋት ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ምህዳሩን ይበልጥ ለማስፋትና የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንዲጠናከር አበክረን እንሰራለን፡፡
• የፌዴራል ስርዓቱ ወሳኝ ሚና እየተጫወት ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን አሁን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የዜጎች ሕገመንግስታዊ መብቶች ሲጣሱ ይታያል፡፡ ይህ እንዲቆምና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፤ የማንነት ጥያቄዎችም በህግ አግባብ እንዲፈቱ አቋም ላይ ደርሰናል፡፡
• ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ጠንክረን መስራት እንዳለብን ተስማምተናል፡፡
• ስርዓት አልበኝነት ይስተዋላል፡፡ የህግ የበላይነት የተከበረባት አገር እንድትሆን ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል፡፡
• የተሃድሶ እንቅስቃሴው የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ሀገራዊ ለውጡን ወደፊት ማራመድ እንዲችል ወስነናል፡፡