loading
…የአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የደስታ መግለጫ አስተላለፉ

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሴት ትልቅ ሀላፊነት ስትረከብ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ያሉት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ኢትዮጵያ ከሰሞኑ ያደረገችው ጾታዊ ተዋጽዖን የጠበቀ ካቢኔ ምስረታና  የሴት ፕሬዚዳንት ምርጫ ሀገሪቱ ሴቶችን ከማብቃት አኳያ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሯን ያሳያል ብለዋል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት አክለውም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መንግስት እና ለኢትዮጵያ ፓርላማም አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)ዋና ፀሀፊ አምባሳደር ማህቡብ ማዐሊም ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የደስታ መግለጫ ማስተላለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በዲፕሎማሲው መስክ ያላቸውን ትልቅ ዕውቀት እና ልምድ ተጠቅመው የኢትዮጵያን እና የአከባቢዋን ጥቅም በሁሉም መስክ ለማራመድ ይጠቀሙበታል ሲል ኢጋድ አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *