loading
የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 72 ነባር አባላቱን በክብር አሰናበተ

የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 72 ነባር አባላቱን በክብር አሰናበተ

አርትስ 28/03/2011

ፓርቲው ሊቀመንበሩንና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩትን ሀጂ ስዩም አወል እና ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ 72 የድርጅቱን አባላት ያሰናበተው በሰመራ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛ መደበኛ ጉባኤው ነው።

የተሰናበቱት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራርና አባላቱ በክልሉ በነበራቸው የስራ ዘመን ላበረከቱት ሚና የምስጋና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬ ውሎው ያለፉትን 3 አመታት የኦዲት ሪፖርት ገምግሞ ያፀደቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተተኪ አመራሮች ምርጫ ያካሂዳል ተብሏል።

ፓርቲው በዚሁ 7ኛ መደበኛ ጉባዔው አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድርን ሰብሳቢ እንዲሁም ኢንጂነር አይሻ መሃመድን ምክትል ሰብሳቢ  አድርጎ መምረጡ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *