የአውሮፓ ፓርላማ በሚቀጥለው ሳምንት በዘረኝነት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት ላደርግ ነው አለ፡፡
የጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በርካታ ሀገራ እና ተቋማት በጉዳዩ ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥው መወያያት ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡
ህብረቱ በጥቁሮች ላይ የሚደርሰው ጫና እንዲቆም የሚያደርግ አሰራር ለመዘርጋት እና የዘር መድሎ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ቡደኖችን የሚያወግዝ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው በአውሮፓ ህብረት ቁልፍ የሚባሉ ስራዎች የተያዙት ነጭ ቀለም ባላቸው ግለሰቦች ሲሆን ከተመሰረተ ከ60 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የአውሮፓ ኮሚሽን አንድም ጊዜ በጥቁር ተመርቶ አያውቅም፡፡
የኮሚሽኑ ፕዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን በዚህ ውይይት እያንዳንዳችን በደመነፍስ ስናራምደው የነበረውን አድልዎ እንፈትሽበታለን ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ ውይይቱን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ከእንግዲህ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ዘረኝነት የሚባል ነገር ቦታ አይኖረውም ሲሉ የማረጋገጫ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
ብላክ ላይቭስ ማተር የሚለው ዓለም አቀፍ ይዘትን የተላበሰው ተቃውሞ በዘር መድሎ የተገፉትን እና ፍትህን የሚሹትን አውሮፓዊያን ሁሉ አነቃንቋል ያሉት ኮሚሽነሯ ለዚህም አጥጋቢ ምላሽ ለመስጠት ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡