loading
የአውሮፓ ህብረት በሰሜን አሪፍካ ያለው ሽብተርተኝነት አሳስቦኛል አለ

አርትስ 04/03/2011

 

የህብረቱ የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ ሀላፊ  ፌዴሪካ ሞጎሮኒ በቀጠናው ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን፣ ሽብርተኝተን ስለመዋጋትና መሰል ጉዳዪች ላይ ለመምከር አልጀሪያ ገብተዋል፡፡

የአልጄሪያ ሬዲዮ እንደዘገበው ሞጎሮኒ ህገ ወጥ ስደትን ከአልጀሪያ መንግስት ጋር በጋራ መከላከል በሚቻልበት ሀሳብ ዙሪያም ይመክራሉ፡፡

ሞጎሮኒ ከአልጀሪያው የውጭ ዳጉይ ሚኒስትር አብደልቃድር ሜሳል ጋር በሊቢያ ምስራቃዊ አካባቢ ስላለው የፀጥታ ጉዳይ እንዲሁም በህብረቱና በአልጀሪያ መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት አንስተው ይወያያሉ ነው የተባለው፡፡

በጣሊያን ፓሌርሞ ከተማ እየተካሄደ ያለው ኮንፈረንስ ለሊቢያ ተፋላሚ ሀይሎች መግባባት እንዲፈጥሩ መልካም አጋጣሚ ነው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሃላፊዋ በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በጋራ መስራ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በአልጄሪያ እና በአውሮፓ ህብረት  መካከል ያለው አጋርነት ለሰሜን አፍሪካና አካባቢው ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ እና  በህብረቱ መካከል ያለውን ንኙነት ለማጠናከር ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል ሞጎሮኒ፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *