የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012 የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቀየኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ጽ/ቤትም የበጀት ዓመቱ ለመጠናቀቅ በሚቀሩት ሶስት ወራት ውስጥ ለሚኖሩት ሥራዎች የሚያስፈልገውን ወጪ በማብቃቃትና በቁጠባ በመጠቀም ከተመደበለት መደበኛ በጀት የሚቀነስ የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለዚህ ሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥም አስታውቋል ፡፡ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት መወሰናቸው የፕሬዝዳነት ፅህፈት ቤት መረጃ አስታውቋል ፡፡
በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮት ለመቋቋም የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን የፕሬዝዳንት ፅህፈት አስታውቋል፡፡ለዚህም ስኬታማነት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዓይነትም ሆነ በገንዘብ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ መቅረቡን ነው የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ያስታወቀው፡፡