loading
የኔፓል  ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደረጉ  ነዉ፡፡

የኔፓል  ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደረጉ  ነዉ፡፡

ምክትል ጠቅይ ሚኒስተሩ ኡፔነድራ ያዳቫ እና የፓርላማ አባሎቻቸው ከጤና ሚኒስትር ጋር  በመሆን  ጉብኝታቸዉን  በኦሮሚያ ክልል ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት በክልሉ ያለውን የጤናው ዘርፍ አገልግሎት አስጣጥ ከጤና ቢሮ እስከ ጤና  ኬላ ድረስ በመዝለቅና በመመልከት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ማቀዳቸው ተነግሯል፡፡

ጎበኝዎቹን  የተቀበሉት የጤና ሚኒስትር ደኤታዋ ወ/ሮ ሰሀረላ አቡደላሂ እንደተናገሩት ሀገራችን በእናቶች ጤና፣ በወረዳ ትራንሰረፎርሜሽንና በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም እያስመዘገበች ያለችው ለውጥ አመርቂ  መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተሞክሮ ወደ ሀገራችሁ በመውሰድ እንደምትተገብሩትና ሀገራችንም ከኔፓል የምትማረው ብዙ ነገር እንዳለም እምነት አለን ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸዉ  በውይይቱም ወቅት የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት አሰጣጥና የጤና ስርአት አተገባበር አስመልክቶ ገለፃ ተደርጎላቸዋል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *