loading
የብድር እጦት የኬንያን ግብርና ማምረቻ ኢንደስትሪ እግር ከወርች አስሮታል

የኬኒያ ብሄራዊ ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተዉ በሃገሪቱ 85 በመቶ ብድር ለግለሰቦች የሚሰጥ ሲሆን አንድ በመቶ የሚሆነዉ ብድር ብቻ ለግብርና ዘርፍ የሚዉል ሆኖ 0.16 በመቶ ብድር ደግሞ ለማምረቻዉ ዘርፍ ይመደባል፡፡

በኬኒያ የግብራናና የማምረቻ ዘርፉ በሚፈለገዉ ልክ የማይደገፍ በመሆኑም ሃገሪቱ ለከፋ የምግብና የሃገር ዉስጥ ምርት እጥረት እንዲጋረጥባት አድርጓታል፡፡

የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የግብርና ዘርፍ ምልከታ በሚለዉ የጥናት ሪፖርት  የግብርናዉ ዘርፍ በመደበኛዉ የባንክ ሴክተር እይታ አስጊ የሚባል ነዉ ሲል ኢስት አፍሪካን የሃገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *