loading
የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት  ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ስነ ስርዓት ዝርዝር መርሃ ግበር ይፋ ሆነ፡፡

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት  ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ስነ ስርዓት ዝርዝር መርሃ ግበር ይፋ ሆነ፡፡

የቀድሞው ፕሬዝዳንት የቀብር ስነስርዓት የመንግስት ከፍተኛ ባላስልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው በጴጥሮስ-ወ-ፓውሎስ መካነ መቃብር እሁድ ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓም ከቀኑ በ9:00 ስዓት ይፈፀማል።

እስከ ግብዓተ መሬቱ ድረስ የሚከተሉት ስነስርዓቶች ይከናወናሉ።

ነገ ቅዳሜ ሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓም ከንጋቱ 11:55 ቤተሰቦችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት የአስከሬን አቀባበል ስነስርዓት ይካሄዳል።

እሁድ ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓም ከጧቱ 1:00 ስዓት ጀምሮ እስከ 5:30 ባለው ጊዜ በሆስፒታልና በመኖሪያ ቤታቸው የተለያየ ዝግጅት ይካሄዳል።

ከቀኑ 5:30 ጀምሮ ስስከ 8:00 ስዓት ድረስ አስከሬኑ በሚሊኒየም አዳራሽ ኦፌሴላዊ የአስከሬን አሸኛኘት ስነስርዓት ይደረግለታል።

ከ8:00 ስዓት ጀምሮ አስከሬኑ ከሚሊኒየም አዳራሽ ተነስቶ አዲስ አበባ ወደ ሚገኘው ጴጥሮስ-ወ-ፓውሎስ መካነ መቃብር እንዲደርስ ይደረጋል።

በመካነ መቃብር ስፍራው የሚካሄዱ ዝግጀቶች እንደተጠናቀቁ የግብዓተ መሬቱ ስነስርዓት በ9:00 ስዓት ይፈፀማል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *