loading
የሶስት ወሯ ህጻን ከዓለም መሪዎች ጋር ተሰበሰበች

አርትስ 15/01/2011
የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን ኒው ዮርክ ላይ በተዘጋጀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ የ3 ወር ሴት ልጃቸውን ይዘው ነበር የተገኙት፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው የጠቅላይ ሚኒስትሯ ልጅ በዚህ እድሜ በዚህ ቦታ የተገኘች የመጀመሪያዋ ህጸን ሆናለች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን ከወሊድ ፈቃድ ወደ ስራ የተመለሱት ባለፈው ነሀሴ ወር ሲሆን ከወለዱ በኋላ በዓለም አቀፍ መድረክ ሲገኙ ይህ የመጀመሪያቸው መሆኑም ታውቋል፡፡
አርደን ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ልጃቸውን የመንከባከቡን ስራ የሚሰሩት አብረዋቸው የተጓዙት ባለቤታቸው ክላርክ ጌይፎርድ ናቸው፡፡
አሁን ላይ በ3 ወሯ ከዓለም መሪዎች ጋር የተሰበሰበችው ይህች ህጻን የዓለም መገናኛ ብዙሀንን ቀልብ በእጅጉ እንደሳበች በስፋት እየተወራላት ይገኛል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *