loading
የሱዳኑ ኡማ ፓርቲ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ከሚገኘው ወታደራዊ ሃይል ጋር በአጋርነት እንደማይሰራ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 የሱዳኑ ኡማ ፓርቲ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ከሚገኘው ወታደራዊ ሃይል ጋር በአጋርነት እንደማይሰራ አስታወቀ፡፡
ፓርቲው በሰጠው መግለጫ በሲቪልና ተወካዮችና በወታደራዊ ሃይሉ መካከል ያልው ግንኙነት ከተሳትፎ በዘለለ በአጋርነት ደረጃ መሆን የለበትም ብሏል፡፡ የነፃነትና የለውጥ ሃይሎች አባል የሆነው ኡማ ፓርቲ የዚህ ፖለቲካዊ ጥምረት ትልቁ ምሶሶ ተደርጎ እንደሚቆጠር ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡

የፓርቲው ዋና ፀሃፊ አል ዋቲቅ አል ብሬየር እነዘኒህ ወታደራዊ ሃይሎችን በአጋርነት እዲሰሩ ማድረግ ህገ መንግስቱን ለነሱ በሚያመቻቸው መንገድ እንዲፈነጩበት መፈቀድ ነው ብለዋል፡፡ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡራሃን በ2011 የሲቪል አስተዳደር አባላትን ከስልጣን ካገዱ ወዲህ በሀገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋትና የህዝብ ቁጣ መበራከቱ ነው የሚነገረው፡፡


ናሽናል ኡማ ፓርቲ በበኩሉ በመፈንቅለ መንግስት የተያዘው ወታደራዊ አስተዳደር በሲቪል እንዲተካና ወታደሮቹ ወደጦር ሰፈራቸው እንዲመለሱ በመግለፅ ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ሀሳብ የሚደግፉ በርካታ ሱዳናዊያንም የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎችን በማካሄድ ከእንግዲህ ሀገራቸው በወታደራዊ ስልጣን መመራት እንደሌለባት መግለጻቸውን ተከትሎ በተደጋጋሚ ከፀጥታ ሃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ሲገቡ ታይተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *