loading
የሰላም አምባሳደር እናቶች ልዑካን ቡድን አፋር ገብቷል

አርትስ 19/03/2011

ቡድኑ ባህርዳር እና መቀሌ ላይ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ከአፋር ቀጥሎ ጋምቤላና አሶሳ ቀጣይ መዳረሻው ይሆናል።

የሰላም ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዘሪሁን ዘውዴ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ከዘጠኝ ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጣው የሰላም አምባሳደር እናቶች ቡድን በትናንትናው እለት መቀሌ ላይ ቆይታ አድርጓል።

በቆይታው ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና  ከክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ የምስራች ብርሃኑ ጋር ተወያይቷል።

ምክትል ርዕሰመስተዳድሩ ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል የክልሉ መንግስት የሰላም አምባሳደር የሆኑት እናቶች  ይዘውት የመጡትን መልዕክት ተግባራዊ እንደሚያደርግተናግረዋል።

አምባሳደሮቹ የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ አርማ ለሀላፊዎቹ ያበረከቱ ሲሆን፥ በተመሳሳይ የክልሉ መንግስት ይህንኑ አርማ ለአምባሳደር እናቶች አበርክተዋል።

ምክትል አፈ-ጉባዔዋ በበኩላቸው፥ የሰላም አምባሳደሮቹ የያዙት መልዕክት በህዝቦች መካከል ሰላማዊ ግንኙነትና አንድነት እንዲኖር የሚያስችል ነው ብለዋል።

የልዑካን ቡድኑ ከክልሉ ካቢኔ አባላትና ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ተወያይተው ዛሬ ማለዳ አፋር መግባታቸውን ነው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊው የተናገሩት ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *