loading
የምንቃወመው መንግስት እንጂ የምንቃወማት ሀገር ልትኖረን አትችልም::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27 ፣ 2013 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እንደጀግኖች እናቶቻችንና አባቶቻችን ሀገራችንን እናስቀድም ሲሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት 80 ዓመት የአርበኞች ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ነው፡፡ ጀግኖች አርበኞቻችን ሀገራችንን ከአምስት ዓመቱ የኢጣልያ ወረራ ነጻ ያደረጉበትን ቀን ስናስብ ሶስት ቁምነገሮችን እየተማርን ነው ብለዋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

አንደኛው ከሁሉም በላይ ሀገርን ማስቀደም ሲሆን አርበኞቹ ከወቅቱ አስተዳደር ጋር ቅሬታ ቢኖራቸውም የውስጥ መከፋፈልን በማስወገድ ጠላትን ከመከላከል አላገዳቸውም ነው ያሉት፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ለሀገር የሚከፈል ዋጋን ለመክፈል የማንንም ጥሪና ማስተባበር ሳይጠብቁ ሀገርን ለማዳን መዝመት ነው ብለዋል፡፡
ለዚህም ማሳያው በወቅቱ ንጉሱ ውጭ ሀገር እያሉ ዘመቻውን የሚያስተባብር የሀገር መሪና ስራውን ተክተው የሚሰሩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ባልነበሩበት ውቅት አርበኞቻችን በራሳቸው ተነሳሽነት ሁሉንም ነገር መፈጸማቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ሦስተኛው ትልቅ ቁም ነገር ደግሞሀገርን የሚታደገው የዜጎች አንድነት መሆኑ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርበኞች በየአካባቢያቸው በጎበዝ አለቃ እየተመሩ በመዝመት ትግሉን ጀምረውታል ብለዋል፡፡ አርበኞቻችን በወቅቱ ብሔር፣ ቋንቋና እምነት ገደብ ሳይሆንባቸው ሀገር አንድ አድርጋቸው ለአንዲት ሀገር በአንድነት ቆሙ፣ ይህም ፍሬውን በቶሎ እንዲለቅሙት አደረጋቸው ሲሉም አብራርተዋል። የሐሳብ ብዝኃነት የሀገር ዕሴት እንጂ የሀገር ዕዳ መሆን ባለመሆኑ የምንቃወመው መንግሥት ይኖረን ይሆናል፤ የምንቃወማት ሀገር ልትኖረን ግን አትችልም ሰሊሉም አሳስበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *