loading
የማሊ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 የማሊ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ:: የሽግግር ወቅቱ ፕሬዚዳንቱ ባህ ንዳዉ የሀገሪቱ ጠቅላይሚኒስትር አድርገው የሾሙት የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞክታር ኡኔን ነው፡፡ የማሊ የሽግግር መንግስት ሲቪል ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙ ከምእራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ የተጣለበትን ማዕቀብ ለማላላት ሁነኛ መንገድ ሊሆንለት ይችላል ተብሏል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የማሊ ጄኔራሎች ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታን በመፈንቅለ መንግስት ማስወገዳቸውን ተከትሎ ሀገሪቱ ከጎረቤት ሀገራት ጋር እንዳትገናኝ ድንበር መዝጋትን የሚያጠቃልል ማእቀብ ተጥሎባታል፡፡ የማሊ ወታደራዊ መንግስት ከ18 ወራት በኋላ በሀገሪቱ ምርጫ ተካሂዶ የሲቪል መንግስት እንዲመሰረት ቃል መግባቱ በኢኩዋስ በኩል በመልካም ጎኑ ታይቶለታል፡፡

ተቋሙ ሲቪል ጠቅላይ ሚኒስትር የምትሾም ከሆነ ማእቀቡን እንደሚያነሳላት ቃል እንደገባላት የሚታወቅ ሲሆን ይህም ተግባራዊ መሆኑ የማእቀቡን መነሳት ተስፋ ከፍ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሸሙት የ64 ዓመቱ ሞክታር ኡኔ ከዚህ ቀደም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ባሻገር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማሊ አምባሳደር በመሆን ያገለገሉ ልምድ ጠገብ ዲፕሎማት መሆናቸው ይነገርላቸዋከል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *