loading
የማሊ ወታደራዊ አዛዦች ከ18 ወራት በኋላ የሲቪል አስተዳደር ለማቋቋም ወሳኔ አሳለፉ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 የማሊ ወታደራዊ አዛዦች ከ18 ወራት በኋላ የሲቪል አስተዳደር ለማቋቋም ወሳኔ አሳለፉ:: ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታን በመፈንቅለ መንግስተር ከስልጣን አውርዶ ሀገሪቱን እየመራ ያለው የማሊ ወታደራዊ ጁንታ የሲቪል መንገስት ለመመስረት የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል፡፡ የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማሊ ወደ ሲቪል አስተዳደር መመለስ አለባት ቢልም በመፈንቅለ መንግስት አድራጊዎቹ ዘንድ ጊዜው በቂ አይደለም በሚል ውድቅ ተደርጓል፡፡

ወታራዊ አዛዦቹ ከተለያዩ አካላት ጋር ከተወያዩ በኋላ ያወጡት ቻርተር ጊዚያዊ የሽግግር መንግስቱ ፕሬዚዳንት ከሲቪል ወይም ከጦሩ አባላት ሊመረጥ ይችላል ይላል፡፡ ይሄ ሁኔታ ደግሞ ከወዲሁ ጄኔራሎቹ ራሳቸውን በቦታው ሊሾሙ በመፈለጋቸው ነው የሚል ጥርጣሬን ፈጥሯል ነው የተባለው፡፡ ኤም 5-አር ኤፍ ፒ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ ውሳኔውን የሲቪል አስተዳደር ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፍ ብሎታል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ፓርቲው ይህን ያለው በሀገሪቱ ምርጫ ቋሚ የስቪል መንግስ እስኪመሰረት በጊዜያዊነት የሚመራው ያሽግግር መንግስትም በሲቪል ይመራ የሚል አቋም ስላለው ነው፡፡ ፓርቲው በውይይቱ ቢካፈልም በመጨረሻ የወሳኔው አካል እንዳልሆነ በሰጠው መግለጫ ይፋ ማድረጉን ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *