loading
የመንግስት እና የግል ተቋማት የጤና በተሽከርካሪ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ህክምና እንዲሰጡ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡ 

የመንግስት እና የግል ተቋማት የጤና በተሽከርካሪ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ህክምና እንዲሰጡ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡
ይህን ያለው የመድን ፈንድ ኤጀንሲ ነው᎓᎓
በተቋሙ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አለማየሁ እንደተናገሩት የሶስተኛ ወገን መመሪያ እስከ 2 ሺህ ብር ድረስ አሽከርካሪዎች መክፈል እንደሌለባቸው ቢገልጽም አንዳንድ የመንግስት እና የግል የጤና ተቋማት ክፍያ ይጠይቃሉ ብለዋል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ የጤና ተቋማት ህክምና እንዲሰጡ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ነው አቶ ጌታቸው የተናገሩት፡፡
በ2010 ዓ.ም በኢንሹራንስ ኩባንያዎች እና በተቋሙ 1 ሺህ 484 ለሚሆኑ የሞት አደጋ ተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ መከፈሉም የመድህን ፈንድ ኤጀንሲ ገልጿል ኢቢሲ እንደዘገበው᎓᎓

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *